=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
መልካም ነገር እንደስሙ መልካም ነው። ጥሩውም ሁሉ እንደ ጣዕሙ ጥሩ ነው። ሰዎችን በማስደሰት የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች እነዚሁ አስደሳቾች ናቸው። የመልካም ስራዎቻቸውን ፍሬ ከማንም በፊት በነፍሶቻቸው ፣ በባህሪያቸውና በልቦናቸው ያገኙታል። በመሆኑም የልብ እርጋታን ፣ ደስታንና እርካታን ያጣጥማሉ።
ጭንቀት ቢጐበኝህ ወይም ትካዜ ቢነካህ ለሌሎች መልካም ነገር ስራላቸው በጎዋልላቸው ደስታና እረፍት ታገኛለህና። ላጣ ሰው ስጥ ፤ የተበደለን ሰው እርዳ ፤ ለተቸገረ ሰው ድረስለት ፤ የተራበን ሰው አብላ ፤ የታመመን ጠይቅ ፤ አደጋ የደረሰበትን አግዝ ደስታ በዙሪያህ አካቦህ ታገኘዋለህ።
መልካም ስራን መስራት እንደ ሽቶ ሻጭ ፣ ተሸካመሚዋን እና ገዢዋን ታውዳለች። መልካም ስራዎችን በመስራት የሚገኘው ደስታም ልቦቻቸውን በመልካም ስራና በበጐ ተግባራት በገነቡ ሰዎች ልቦች ውስጥ ካሉ መድሃኒት ቤቶች የሚከፋፈሉ የተባረኩ ክኒኖች ናቸው። የፀባይ ድሆችን ብሩህ ፈገግታን ማከፋፈል በእሴቱ ዓለም ውስጥ ያለ ምንዳው የማይቇረጥ ምፅዋት ነው። «መልካም ስራን አትናቅ። ወንድምህን ፈካ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን» ፊትን ማጨፍገግ መነሻውን ከአሏህ ውጪ የማያውቀውን ጦር በሌሎች ላይ እንደ መምዘዝ ነው።
አንዲት ዝሙት አዳሪ አንድን ውሻ አንድ እፍኝ ውሃ ማጠጣቷ ስፋቱ የሰማያትና የምድሮች ያክል የሆነን ገነት አሰጥቷታል። ምክኒያቱም የምንዳው ባለቤት መሃሪ አመስጋኝ መልካም ሰሪና መልካም ስራን የሚወድ ሃብታምና ምስጉን ነው።
የጭንቀት ፣ የድንጋጤና የፍርሃት ጭራቆች የሚያስፈራሯችሁ ሰዎች ሆይ!.... ወደ መልካም ስራዎች ኑ። ሌላውን በመጥቀም ፣ በማስተናገድ ፣ በማፅናናት ፣ በመርዳትና በማገልገል እራሳችሁን አዝናኑ፤ የደስታን ጣእም ፣ ቀለምና ቃና ታገኛላችሁና።
አል-ቁርአን 92:19-21
"ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ ይህንን ሠራ። ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል።"
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|